ፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከቦርድ አባላት ጋር የአሰልጣኞች የደረጃ ዕድገትን በማፅደቅ እና የ9ወር የስራ አፈፃፀም ግምገማ በማድረግ ውይይት አካሄዱ።
System Administrator |
May 24, 2026 at 7:23 AM |
1 month ago |
27 views
ፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከቦርድ አባላት ጋር የአሰልጣኞች የደረጃ ዕድገትን በማፅደቅ እና የ9ወር የስራ አፈፃፀም ግምገማ በማድረግ ውይይት አካሄዱ።
ሚያዚያ10/2018ዓ.ም
የፍ/ዳ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ የ9ወር የስራ አፈፃፀም ሪፖርት "በአቶ አንተነህ ባህሩ" የቀረበ ሲሆን
_ የተቋሙ የት/ስልጠና የመደበኛ ሰልጣኝ በተመለከተ
_ የአጫጭር ስልጠና
_ የውጭ ሃገር ስራ ስምሪት
_ የኢ/ኤ/ድጋፍ አገልግሎት በተመለከተ እና
_ የተቋሙን የውስጥ ገቢ ለማሳደግ የተሰሩ ተግባራትንና በግቢው ስላሉ የወተት ላሞች እርባታ፣ ስለእርሻ ልማት ስራው ፣ስለ ምርት ክፍል ስራዎች እያንዳንዱ ተግባራት በዝርዝር በሪፖርቱ ቀርቦ የተገመገመ ሲሆን አባላቱ ገንቢ ሃሳቦችን እና አስተያየቶችን ሰጥተውበታል።
ኮሌጁ እያሳየ ያለው የስራ እንቅስቃሴ ጥሩ ውጤት የሚያመላክት እንደሆነና ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እዳለባቸው እንዲሁም የተቋሙ አጠቃላይ ሠላተኖች ከፍተኛ የስራ ተነሳሽነትና ቅንነት ያላቸው መሆናቸውን በማመስገን በቀጣይ ከፍተኛ የስራ አፈፃፀም እንደሚታይ ተስፋቸውን ገልፀዋል።
እንደ ቦርድ የሚያስፈልገውን ድጋፍና እገዛ እንደሚያደርጉና በተለይ የሠልጣኝ ቅበላ ላይ በጋራ ተረባርቦ መስራት እንደሚገባ በቦርድ ሰብሳቢው የማጠቃለያ ሃሳብ ተሰጥቶ ውይይቱ ተጠናቋል።
10/08/2018ዓ.ም
ፍ/ዳ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ