ፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በአካባቢው ለሚገኙ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚኖሩ ማህበረሰቦች ለሌማት ትሩፋት ድጋፍ አደረገ።
ፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በአካባቢው ለሚገኙ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚኖሩ ማህበረሰቦች ለሌማት ትሩፋት ድጋፍ አደረገ።
መጋቢት 18/2018ዓ.ም
ፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በግቢው ካመረተው የስንዴ እና የበቆሎ ምርት 10 ኩንታል የሚሆነውን በከተማችን ለሚገኙ 22 አቅመ ደካሞች ለእያንዳንዳቸው 25 ኪሎ ስንዴ እና 25 ኪሎ በቆሎ ለሌማት ትሩፋት መጭው ትንሳኤ በአልን ምክንያት በማድረግ የኮሌጁ አመራሮች እና የዞን ስራ እና ክህሎት መመሪያ ኃላፊ "አቶ አያሌው ያረጋል" እንዲሁም የፍ/ሰላም ከ/አስ/ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ኃላፊዎች በተገኙበት ርክክብ ተደርጓል።
የመምሪያው ሃላፌ እንደተናገሩት ኮሌጁ ከመደበኛ ስራው ጎን ለጎን የማህበረሰብ ችግሮችን ለመጋራት እና ለመፍታት እየተጓዘበት ያለው እርቀት እጅግ የሚያስመሰግን ነው። ከዚህ በፊትም የአቅመ ደካሞችን ቤት በመስራት፣ ለአካባቢው ነዋሪ በእርካሽ ዋጋ የወተት አቅርቦት ፣እና ሌሎችም ተግባራቶቹ ኮሌጁ የሌማት ቱርፋት እና የማዕድ ማጋራትኢኒሸቲቪን በተግባር እየተወጣ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
የኮሌጁ ዲን "አቶ አንተነህ ባህሩ " በበኩላቸው እንደገለጹት ኮሌጁ ከመደበኛ የስልጠና ፕሮግራሙ ባሻገር በተለያዩ ዘርፎች የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶችን እያደረገ እንደሚገኝ እና በቀጣይም ይህ ተግባር ተጠናክሮ እደሚቀጥል ገልፀዋል።
በአጠቃላይ ኮሌጁ የአቅመ ደካሞችን ቤት በመገንባት፣ የተለያዩ የቁሳቁስ ድጋፎችን በማድረግ የማህበረሰቡን ችግር በመጋራት ላይ ይገኛል።
18/07/2018ዓ.ም
ፍ/ዳ/ፖ/ቴ/ኮሌጅኮሌጅ