EN አማ
Back to News
ስልጠና በተግባር ሲደገፍ

ስልጠና በተግባር ሲደገፍ

System Administrator  |  May 24, 2026 at 2:25 PM  |  1 month ago  |  32 views

ስልጠና በተግባር ሲደገፍ

የፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከአልማ ጋር በመተባበር በዶሮ እርባታ ስልጠና እየሰጠ መሆኑ ይታወቃል።
በመሆኑም እነዚህን ሰልጣኞች በንድፈ ሀሳብ እና የተግባር ስልጠና በኮሌጁ ውስጥ ከሚሰጠው ስልጠና በተጨማሪ ይበልጥ እውቀታቸውን ለማዳበር በዘርፉ ከተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ጋር በመሄድ  ከስልጠና ባሻገር  የስራው አለም ምን ይመስላል የሚለውን በከተማችን ውስጥ በዶሮ እርባታ ዘርፍ አንቱ ከተባሉት ከአቶ ጌታሰው ኢንተርፖራይዝ በመሄድ እንዲሰለጥኑ ተደርጉዋል።
አሰልጣኝ ሙላት ማተቤ እና አሰልጣኝ አብርሀም እንደተናገሩት በንድፈ ሀሳብ የሰለጠኑትን ስልጠና በተግባር ምን እንደሚመስል ሲመለከቱ የበለጠ ተነሳሽነትና እንዲኖራቸው እና ተጨማሪ እውቀት እንደሚያገኙበት አስረድተዋል።
የድርጅቱ ባለቤት አቶ ጌታሰውም የዶሮ እርባታ ከምንም በላይ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልገው እና አጠቃላይ የጤና አጠባበቅ እና አመጋገብ ስርዓት ላይ ያለውን እውቀት ለሰልጣኞች ግንዛቤ ፈጥረዋል።
በቦታው ተገኝተው ስልጠናውን የተከታተሉት የኮሌጁ ት/ስ/ም/ዲን አቶ ቸኮል አየለም ይህ ስልጠና እንዲሰጥ ለተባበሩን አቶ ጌታሰውን አመስግነው ኮሌጁ ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር በትብብር ስልጠና አብሮ እንደሚሰራ አስታውቀዋል።

መጋቢት  29/2018
ፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

Previous | Next