EN አማ
Back to News
ለቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ዲኖች፣ ዞኖች፣እና የክልል ክላስተር አስተባባሪዎች እና ዞን  በዲጂታል አማራ ኢኒሼቲቭ የዲጅታል ስኪል ስልጠና አፈጻጸም ላይ የተሰጠ ግብረ-መልስ

ለቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ዲኖች፣ ዞኖች፣እና የክልል ክላስተር አስተባባሪዎች እና ዞን በዲጂታል አማራ ኢኒሼቲቭ የዲጅታል ስኪል ስልጠና አፈጻጸም ላይ የተሰጠ ግብረ-መልስ

Sintayehu  |  June 8, 2026 at 4:36 AM  |  1 month ago  |  40 views

ለቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ዲኖች፣ ዞኖች፣እና የክልል ክላስተር አስተባባሪዎች እና ዞን 
በዲጂታል አማራ ኢኒሼቲቭ የዲጅታል ስኪል ስልጠና አፈጻጸም ላይ የተሰጠ ግብረ-መልስ 
1. በምዝገባ አፈጻጸም (Plan vs. Enrollment) ላይ የተሰጠ ሃሳብ
•ኮሌጆች ለአካባቢው ወጣቶችና ማህበረሰብ የ2 ሳምንት የተጠናከረ የምዝገባ ንቅናቄ በመፍጠር ምዝገባውን ኮሌጆች አሁን ካሉበት እቅዱ 100% እንዲያሳድግ ማድርግ።
2. ከምዝገባ ወደ ስልጠና ሽግግር (Training Commencement) ላይ የተሰጠ ሃሳብ
1. የወርክሾፕ አጠቃቀምን በፈረቃ ማደራጀት (Multi-Shift Scheduling):
oየተመዘገቡ፣በመመዘገብ ላይ ያለትን ሰልጣኞች በፍጥነት ወደ ክፍል ለማስገባት ያሉትን የኮምፒውተር ላብራቶሪዎች በ4 ፈረቃዎች (በጠዋት፣ ከሰዓት፣ በምሽት እና በቅዳሜና እሁድ) በመደልደል መስራት ይጠበቃል
•የአሰልጣኞች ጊዜያዊ ስምሪት (Trainer Mobilization): ዝቅተኛ አፈጻጸም ባላቸው ኮሌጆች ውስጥ ያለውን የአሰልጣኞች መልሶ ማደረጀትና ስምሪት በመስጠት በየ3 ቀኑ መገምገም እና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ፡፡ 
•የእርስ በርስ የምክር ድጋፍ ትስስር (Institutional Mentorship): ዳካማ አፈጻጸም ያላቸውን ከጠንካራ አፈጻጸም ካላቸው ተቋማት ጋር በማጣመር ሰልጣኞችን በፍጥነት ወደ ስልጠና ለማስገባት የተጠቀሙበትን የወርክሾፕ አደረጃጀትና የክትትል ስልት በ3 ቀናት ውስጥ ልምድ በመለዋወጥ ወደ ስራ መግባት።
•ኮሌጆች የተለያዩ የፕሮሞሽንና ቅስቀሳ ስልቶችን ለምሳሌ፡ የኤስኤምኤስ (SMS) የጥሪ መልዕክት ማስተላለፍ፣የአካል ጉብኝት እና ተከታታይ ክትትል ማድረግ

3. የክትትልና የሪፖርት አቀራረብ ማሻሻያዎች (Monitoring & Reporting)
የቢሮው፣ዞንና ኮሌጅ አመራርና ባለሙያ ሪፖርት ትኩረት ማድረግ ያለበት፡
• ምዘገባ vs ስልጠና እና ቀጥሎ ሰርትፊኬት በሚል ሳምንታዊ ሪፖርቶችንመከታተል
• ከምዝገባ ቁጥር ወደ ስልጠና አጀማመር (Conversion Rate) ብሎም ሰርትፊኬት ላይ ትኩረት ማድረግ፣ 
•የእነዚህ ዝቅተኛ አፈጻጸም ያላቸው ኮሌጆች በየሳምንቱ 3 ቀን በመገምገም 100% እንዲሳካ ጥብቅ መካታተል የስፈልጋል።
ቢሮው

Previous | Next