የፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ችግኝ ተከላ ፕሮግራም
Sintayehu |
June 22, 2026 at 6:50 PM |
29 days ago |
45 views
የፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከደ/ማርቆስ ብቃት ማረጋገጫ ማዕከል አስተባባሪዎች እና ከመዛኞች ጋራ ተመዛኝ ተማሪዎችን በመያዝ ለችግኝ መትከያ የሚሆን የጉርጓድ ቁፋሮ ስራ ተከናውኗል።
ሰኔ15/2018ዓ.ም
👉ኮሌጁ በያዝነው የክረምት ወራት ከአራት ሺ/4000/በላይ ችግኞችን ለመትከል በእቅድ የያዘ ሲሆን በዛሬው ዕለት ከ120በላይ ተሳታፊዎች በተገኙበት ሁለት መቶ/200/ የችግኝ መትከያ ጉርጓድ መቆፈር ተችሏል።
👉ይህ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና በተዘጋጀው ስፍራ ችግኞችን በመትከል የተያዘውን ዕቅድ ማሳካት እንደሚገባ በኮሌጁ ም/ዲን "በአቶ ቸኮል አየለ" መልዕክት ተላልፏል።
👉ተመዛኝ ተማሪዎች እና ተመራቂዎች በዚህ ታላቅ ተግባር ላይ በመሳተፍ አሻራቸውን ማስቀመጣቸው ጥሩ አጋጣሚ እንደሆነ እና ታላቅ ደስታ እንደፈጠረላቸውም ገልፀዋል።
15/10/2018ዓ.ም
ፍ/ዳ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ