EN አማ
Back to News
የፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አመታዊ የስራ አፈፃፀም ግምገማ አደረጉ

የፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አመታዊ የስራ አፈፃፀም ግምገማ አደረጉ

Sintayehu  |  July 10, 2026 at 4:15 PM  |  11 days ago  |  13 views

የፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አመታዊ የስራ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ።

03/11/2018ዓ.ም

በፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2018ዓ.ም አመታዊ የስራ አፈፃፀም ግምገማ ተካሂዷል። በዕለቱ ዝርዝር የስራ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በጥንካሬ መቀጠል ያለባቸው እና በቀጣይ መሻሻል የሚገባቸው ተግባራትን በማንሳት ጥልቅ ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱ፦ 
👉 የኮሌጁን ውስጥ ገቢ እንዲያዳብሩ እና ለማሰልጠኛ እንደ ጥናትና ምርምር እንዲያገለግሉ የተቋቋሙ የተለያዩ ፕሮጀክቶች/ የወተት ላሞች እርባታ፣ የእርሻ ልማት ስራ፣ የደሮ እርባታ፣ የመሠረተ ልማት ኮሚቴ እና ሌሎችም/ ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ከቤቱ አስተያየት ተሰጥቷል።
👉 ሌላው አዲስና ነባር ሰልጣኝ ቅበላ አፈፃፀሙን  በቀጣይ የዘጠና ቀናት እቅድ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራ፤
👉 የስልጠናን ጥራት ከማስጠበቅ አኳያ
👉አጠቃላይ የፋይናስ እንቅስቃሴ ጥሩ እደሆነ 
 👉የሠራተኞች ጥቅማጥቅም በተመለከተ 
👉 የግብውን ውበት፣ የመሠረተ ልማት እና ኮሊደር ስራ በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶት ቢሰራ ሚሉ እና ሌሎች ሃሳቦች ተነስተው ውይይት ከተደረገባቸው በኋላ ለቀጣይ አቅጣጫ ተሰጦባቸዋል።

በአጠቃላይ በነበረው የአፈፃፀም ግምገማ የተቋሙ እንቅስቃሴ ጥሩ በሚባል ደረጃ ላይ እንደሆነ እና በመጪው በጀት አመት ከዚህ የበለጠ ለመስራት መትጋትና በእኔነት ስሜት በጋራ በመሆን ለላቀ ውጤት መስራት ይጠበቅብናል በማለት የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን ጨምሮ በኮሌጁ ዲን " በአቶ አንተነህ ባህሩ" የማጠቃለያ ሃሳብ ግምገማው ተጠናቋል።

ሐምሌ03/2018ዓ.ም
ፍ/ዳ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ

Previous | Next