እኛው ለእኛ
Sintayehu |
July 16, 2026 at 4:34 PM |
5 days ago |
8 views
«እኛ ለእኛ» ማለት ራስን በራስ የመደገፍና የውስጥ አቅምን በተግባር የመተርጎም ታላቅ መርህ ነው። ለዚህም ዋነኛው ማሳያ በኮሌጃችን ውስጥ የዶሮ እርባታውን በራሳችን ከማስተዳደር ባለፈ፣ ለዶሮዎቹ የሚያስፈልጉ መጋቢዎችን (መመገቢያዎችን) እኛው ራሳችን ጥረንና ግረን ማምረታችን ነው። ይህ ዓይነቱ ተግባራዊ እንቅስቃሴ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የወረቀት ላይ ዕውቀት ብቻ ሳይሆን፣ የዕለት ተዕለት ፍላጎቶችን በራስ አቅም መሙላትና ራስን በራስ የመቻልን ትርጉም በተጨባጭ ማሳየት የሚችሉበትን አቅም በተግባር ያረጋገጠ ነው።
«ቴክኒክና ሙያ የቴክኖሎጂ መፈልፈያ ነው» ስንል በባዶ ምኞት ሳይሆን በእንዲህ ዓይነት በማስረጃ በተደገፉና በሚታዩ ውጤቶች ነው። ይህ ስኬት ኮሌጃችን ለወደፊት እቅዶች ብቻ ሳይሆን፣ በአሁኑ ሰዓት የኮሌጃችንንና የአካባቢያችንን ማህበረሰብ የሚፈትኑ ችግሮችን በፈጠራ ለመፍታት ያለውን የጸና ቁርጠኝነት በግልጽ ያሳያል። ወደፊትም የማህበረሰባችንን ህይወት የሚያቀሉና ችግሮችን በዘላቂነት የሚቀረፉ ቴክኖሎጂዎችን ያለማቋረጥ ለማፍለቅና ለማምረት በትኩረት እንሰራለን።