ለኮሌጃችን ዘርፍ ተጠሪዎች በሙሉ፤
ለኮሌጃችን ዘርፍ ተጠሪዎች በሙሉ፤
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️
ሰልጣኞቻችሁ የብቃት ማረጋገጫ (COC) ምዘናን በከፍተኛ ውጤት እንዲያልፉ ለመርዳት የሚያስችል አዲስ እና ዘመናዊ ኦንላይን ፕላትፎርም በ https://fdcollege.edu.et/lms/login ድረ-ገጽ ላይ በይፋ አዘጋጅተናል። ይህ ሲስተም የቴክኒክና ሙያ ተቋማት እንዲሁም የተለያዩ የስልጠና ማዕከላት የራሳቸውን የሞዴል ጥያቄዎች በቀላሉ መጫን የሚችሉበት ምቹ አሰራር አለው። በዚህም ምክንያት ሰልጣኞችዎ ከዛሬ ጀምሮ ወደተለያዩ ዘርፎች የተከፋፈሉትን ፈተናዎች በሊንኩ በኩል ማግኘትና መለማመድ ይጀምራሉ።
ይህ ፕላትፎርም ሰልጣኞችዎ ስልካቸውን ብቻ በመጠቀም ባሉበት ቦታ ሆነው በተመቻቸው ሰዓት እንዲፈተኑ ሙሉ ነጻነት ይሰጣቸዋል። የፈተናውን ድባብ አስቀድመው እንዲለምዱት የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ ያመጡትን ውጤትና የጎደላቸውን እውቀት ወዲያውኑ በስልካቸው ማየት ይችላሉ። ይህም ሰልጣኞቹ ያለምንም ስጋትና እንግልት ለዋናው የCOC ምዘና ራሳቸውን በሚገባ እንዲያዘጋጁ ትልቅ እገዛ ያደርጋል።
በመሆኑም ከኮሌጃችን ተጨባጭ ሁኔታና ከምትሰጧቸው የስልጠና ዘርፎች ጋር የሚስማሙ የሞዴል ጥያቄዎችን በፕላትፎርሙ ላይ በመጫን የሰልጣኞቻችሁን የውጤታማነት ደረጃ አሁንኑ ማሳደግ ትችላላችሁ። ይህንን ዘመናዊ የፈተና መለማመጃ ሲስተም መጠቀም ለመጀመርና የባለቤትነት አካውንት ለመክፈት ዛሬውኑ በ https://fdcollege.edu.et/lms/login በኩል ይግቡ ወይም ያነጋግሩን።
የኮሌጁ ዲጂታላይዜሽን ኮሚቴ
"ዲጂታል ማህበረሰብ በመፍጠርና የስልጠና ጥራትን በማረጋገጥ ሁላችንም የበኩላችንን ድርሻ እንወጣ!!"
ወደ ፊት በተለይ ለስልጠና ጥራት አጋዥ የሆኑ አዳዲስ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ይዘን ከተፍ የምንል መሆኑን ከወዲሁ እንገልጻለን።