የፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የአረንጓዴ ልማት እና የተሻሻሉ የፍራፍሬ ዝርያዎች እንክብካቤ እንቅስቃሴ
Sintayehu |
July 29, 2026 at 6:55 AM |
1 month ago |
46 views
የፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የአረንጓዴ ልማት እና የተሻሻሉ የፍራፍሬ ዝርያዎች እንክብካቤ እንቅስቃሴ
ፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በአካባቢ ጥበቃ እና በአረንጓዴ ልማት ስራዎች ላይ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ሰፊ እንቅስቃሴዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል። ኮሌጁ ተቋማዊ አካባቢውን ለማስዋብ እና ለምግብ ዋስትና አስተዋጽኦ ለማበርከት በማለም የተሻሻሉ የማንጎ እና የአቦካዶ ተክሎችን በግቢው ውስጥ በመትከልና ጥንቃቄ የተሞላበት እንክብካቤ በማድረግ ላይ ይገኛል።
በሐምሌ 20/2018 ዓ.ም በተከናወነው ተግባርም ኮሌጁ ተጨማሪ 200 (ሁለት መቶ) የተሻሻሉ የማንጎ ዝርያ ያላቸውን ተክሎች ወደ ግቢው በማስገባት የተክሎችን ቁጥር አሳድጓል። የኮሌጁ ዋና መመርያ ተክሎችን መትከል ብቻ ሳይሆን፤ ተክሎቹ አድገው ለተፈለገው ውጤት እስኪበቁ ድረስ ቀጣይነት ያለው ውሃ አቅርቦት፣ ጥበቃ እና ሁለንተናዊ እንክብካቤ ማድረግ ነው።
በአጠቃላይ ፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተግባር የተደገፈ የአካባቢ ልማት በመተግበር ተቋማዊ ውጤታማነትን ለማሳደግ እየሰራ ይገኛል። ይህ እንቅስቃሴ የአካባቢ ጥበቃ ባህልን በማጠናከር ለወደፊቱ አረንጓዴ፣ ለም እና ተስማሚ የሆነ የተቋም ግቢን ለመፍጠር ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል።