ለሁሉም ቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጆች የግብዣ ጥሪ
ለሁሉም ቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጆች የግብዣ ጥሪ በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት (FTVTI) ለሚዘጋጀው ዓለም አቀፍ የምርምር እና ቴክኖሎጂ ውድድር
በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት (FTVTI) አዘጋጅነት የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የምርምር እና የቴክኖሎጂ ውድድር ምዝገባ መጀመሩን ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው። በመሆኑም በየኮሌጁ ለውድድር የሚሆኑ ቴክኖሎጂዎች በመምረጥ ኮሌጃችሁንም ክልላችሁንም እንድታስጠሩ እንዲሁም እራሳችሁም እድትጠቀሙ እያሳሰብን ቀኑ አጭር ስለሆነ ቶሎ ተመዝገቡ
የውድድሩ ዘርፎች፦
ታዳሽ ኃይል እና አረንጓዴ ቴክኖሎጂዎች
ዘመናዊ ማኑፋክቸሪንግ እና የኢንዱስትሪ አውቶሜሽን
ግብርና እና አግሮ-ፕሮሰሲንግ ቴክኖሎጂዎች
የመረጃ ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) እና ዲጂታል ፈጠራ
ኮንስትራክሽን እና የዝቅተኛ ዋጋ ቤቶች ቴክኖሎጂዎችቴክኖሎጂዎችቴክኖሎጂዎችቴክኖሎጂዎች
የተሳትፎ ጥቅሞች፦
ከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት (በዶላር)፤
ከዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ጋር አብሮ ለመሥራት የሚያስችል ዕድል፤
የፈጠራ ስራዎን በዓለም አቀፍ መድረክ የማስተዋወቅ ዕድል።
ተሳታፊዎች በውድድሩ ላይ በአካል በመገኘት ወይም በበይነ-መረብ (Virtually) መሳተፍ ይችላሉ።
የምዝገባ ሊንክ (Link): https://irctc.ftveti.edu.et/
ማሳሰቢያ፦ የክልላችሁ/የተቋማችሁ አመራሮች መረጃውን ለሁሉም ኮሌጆች እና ባለሙያዎች በማጋራት አቅም ያላቸው ዜጎች እንዲወዳደሩና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ትብብራችሁን እንጠይቃለን።
ለተጨማሪ መረጃ በዌብሳይቱ ላይ የሚገኙ ዝርዝሮችን ይመልከቱ።