EN አማ
Back to News
ፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለዳሞት መሰናዶ ቁጥር 2 የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ያዘጋጀውን የአምስት ቀናት ልዩ ልዩ ስልጠና በዛሬው ዕለት ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ አስጀምሯል።

ፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለዳሞት መሰናዶ ቁጥር 2 የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ያዘጋጀውን የአምስት ቀናት ልዩ ልዩ ስልጠና በዛሬው ዕለት ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ አስጀምሯል።

Sintayehu  |  August 11, 2026 at 12:39 PM  |  24 days ago  |  46 views

ፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለዳሞት መሰናዶ ቁጥር 2 የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ያዘጋጀውን የአምስት ቀናት ልዩ ልዩ ስልጠና በዛሬው ዕለት ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ አስጀምሯል። ይህ ስልጠና ተማሪዎቹ ከፈተና በኋላ ወደ ቀጣዩ የሕይወት ምዕራፍ ከመሸጋገራቸው በፊት ጠቃሚ የሆኑ ክህሎቶችን እንዲጨብጡ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

በዚሁ መሠረት ተማሪዎቹ በአምስቱ ተከታታይ ቀናት ውስጥ የሕይወት ክህሎት (Life Skills)፣ የሥራ ፈጠራ (Entrepreneurship)፣ ዲጂታል አማራ እና የኢትዮ ኮደርስ (EthioCoders) ስልጠናዎችን የሚከታተሉ ይሆናል። እነዚህ ስልጠናዎች ተማሪዎች በቴክኖሎጂና በፈጠራ የታገዘ እውቀት ኖሯቸው ለነገው ማንነታቸው ጠንካራ መሠረት እንዲጥሉ ትልቅ እገዛ ያደርጋሉ።

የዛሬውን የመጀመሪያ ቀን መርሃ ግብር የኮሌጁ ዲን አቶ አንተነህ ባህሩ እና ምክትል ዲኑ አቶ ቸኮል አየለ በጋራ በመሆን የከፈቱት ሲሆን፣ ለተማሪዎቹ ስለ ስልጠናው ዓላማና ጠቀሜታ ሰፊ ግንዛቤ ፈጥረውላቸዋል። ተማሪዎቹም ማብራሪያውን ካዳመጡ በኋላ በመጀመሪያው ዙር የሚሰጠውን የሕይወት ክህሎት (Life Skills) ስልጠና በከፍተኛ ተነሳሽነት መከታተል ጀምረዋል።

ተማሪዎቹ የአምስት ቀናት ቲዎሪና ተግባራዊ ስልጠናቸውን ሲያጠናቅቁ በኮሌጁ ውስጥ የሚገኙ ልዩ ልዩ የቴክኖሎጂ ወርክሾፖችን የሚጎበኙ ይሆናል። ከዚህም በተጨማሪ በኮሌጁ እየተከናወኑ ያሉትን እንደ የዶሮ እርባታ፣ የወተት ላሞች እንክብካቤ እና የተለያዩ የእርሻ ሥራ ፕሮጀክቶችን በመጎብኘት በተግባር የተደገፈ ሰፊ ልምድ እንደሚቀስሙ ተገልጿል።

Previous | Next