ፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለስራ ፈላጊ ወጣቶች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
ፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለስራ ፈላጊ ወጣቶች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
06/12/2018ዓ.ም
ፍ/ዳ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ
ፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከፍኖተሰላም ከተማ አስተዳደር አልማ ብቁ ወጣት ፕሮጀክት ( Master Card Foundation) ጋር በመተባበር 130 ወጣቶች ለ2ኛ ዓመት 1ኛ ዙር በተለያዩ የሙያ ዘርፍ ስልጠና መስጠት ጀመረ።
ከስልጠናው ተሳታፊዎች መካከል 10% አካል ጉዳተኞች 80 % ሴቶች እንደሆኑ በፕሮጀክቱ አስተባባሪ ተገልጿል።
ኮሌጁ በደሮ እርባታ፣ ንብ ማነብ፣ የጥልፍ ስራ፣ማድለብ እና ባልትና ውጤቶች ምርት ላይ ስልጠና ይሰጣል፣ ፕሮጀክቱ ሰልጣኞችን አእስከ ስራ መፍጠር የቁሳቁስ እና ሌሎች ድጋፎች እንደሚደረግላቸው የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ዳግማዊ ገልፀዋል።
የስልጠናውን መርሃግብር በይፋ የከፈቱት የፍኖተሰላም ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ እና የአልማ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዮናስ ሞላ አልማ ከተለያዩ ፕሮጀክቶች ጋር በመተባበር ግንባታ ከመገንባት ባለፈ በወጣቱ አዕምሮ ልማት ላይ እየሰራ ያለውን ስራ አመስግነዋል ።
ስልጠናው ፍላጎትን መሠረት ያደረገ በመሆኑ የስራ ዕድል መፍጠሪያ በር እንጅ ራሱ የስራ ዕድል አይደለም ያላችሁን እውቀት እና ዕምቅ ችሎታ በመጠቀም የመለወጥ ችሎታ ባላችሁ ስነልቦና ግንባታ ይወሰናል ።አዕምሯችሁን፣አካባቢያችሁን እና ፀጋዎችን በመጠቀም ለመለወጥ ስልጠናውን በአግባቡ መውሰድ አለባችሁ ሲሉ አቶ ዮናስ ተናግረዋል ።
የፍኖተሰላም ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገድፈው ጌታቸው ለበርካታ ወጣቶች የስራ ዕድል እንደሚፈጥሩ ገልፀው ስልጠናው የይስሙላ ሳይሆን የለውጣችሁ መነሻ ምዕራፍ ነው። ስልጠናውን ወደተግባር በመቀየር የሚሰጣችሁን መነሻ ካፒታል መጠቀም ወደስራ መግባት አለባችሁ በማለት አሳስበዋል።