የፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የበጎ አድራጎት ስራ
Sintayehu |
August 26, 2026 at 3:54 PM |
9 days ago |
24 views
ፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በፍ/ሰላም ከተማ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ማህበረሰቦች ድጋፍ አደረገ።🇪🇹🇪🇹🇪🇹
20/12/2018ዓ.ም
ፍ/ዳ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ የህ/ግንኙነት ቡድን
ፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በፍ/ሰላም ከተማ ለሚገኙ አቅመ ደካሞች የስንዴ ድጋፍ እና የማዕድ ማጋራት(የምሳ ግብዣ) በማድረግ የማህበረሰቡን ችግር በመጋራት የበጎ አድራጎት ስራውን አጠናክሮ እየሰራ ይገኛል።
ኮሌጁ ከመደበኛ ስራው ጎን ለጎን በርካታ ስራዎችን የሚያከናውን ሲሆን በበጎ አድራጎት ስራው ከዚህ በፊት የፈረሱ ቤቶችን በመጠገን፤ የመክፈል ሃቅም ለሌላቸው ሰዎች በየአመቱ የ10 ሰዎች የጤና መድህን በመክፈል፤ ደጋፊ ወላጅ ለሌላቸው ተማሪዎች ነፃ የትምህርት እድል በመስጠት እና አካል ጉዳተኞችን እና አረጋውያንን የቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ ለአካባቢው ማህበረሰብ አለኝታነቱን እያሳየ የሚገኝ ተቋም ነው።
ይህ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በኮሌጁ ዲን "በአቶ አንተነህ ባህሩ" ተገልጿል።
"ፍኖተ ዳሞት የማህበረሰቡ አገልግሎት ሰጪ ተቋም"