ፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ከተመረጡ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር ውይይት አካሄደ
የፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከባለሀብቶች፣ ከማምረቻ ኢንዱስትሪዎች እና ከተመረጡ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት (ሆቴሎች እና የሕክምና ክሊኒኮች) ጋር የስልጠና ሰነድ በማዘጋጀት እና በማቅረብ ውይይት ተካሄደ።
ጥቅምት17/2019ዓ.ም
ፍ/ ዳ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ የህ/ግንኙነት ቡድን
በመድረኩ የፍ/ሰላም ም/ከንቲባ "አቶ ጊዜው ደግአረገ"ተገኝተው ፕሮግራሙን ያስጀመሩ ሲሆን የመወያያ ሰነዱ በፍ/ዳ/ፖ/ቴ/ ኮሌጅ ዲን "በአቶ አንተነህ ባህሩ" ቀርቧል።በመጨረሻም የምዕ/ጎ/ዞን ስራ እና ክህሎት መምሪያ ምክትል ኃላፊ "አቶ አያልሰው ሙሉ"የውይይት መድረኩን በመምራት አወያይተዋል።
ኮሌጁ በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011፣ በ Entrepreneurship ፣ በካይዘን፣ በሙያ ስነ-ምግባር፣ በሥራ ላይ ደህንነት፣ በደንበኞች አያያዝ እና በሙያ ብቃት ማሳደግ ዙሪያ በኩባንያ (In- company) ስልጠና መስጠት እንደሚፈልግ ተገልጿል።
ፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ፍኖተ ሰላም ከተማ የሚገኝ የመንግሥት ቲቪኢቲ ተቋም ሲሆን በመደበኛና በአጭር ጊዜ ስልጠና በኢንዱስትሪ ትስስር እና በሙያ ብቃት ማሻሻያ ላይ ያተኮረ ሥራ እየሰራ ነው።ይህን የኩባንያ ውስጥ ስልጠና በመስጠት የአካባቢውን ኢንዱስትሪዎችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ዝግጁ መሆኑም ተገልጿል።በመጨረሻም አሰሪዎች ስልጠናው እጅግ እንደሚያስፈልግ አንስተው በቀጣይ የሰራተኞቻቸውን ብቃት ለማሻሻል ኮሌጁን እንደ ቁልፍ ማሰልጠኛ ተቋም ልንጠቀመመው ይገባል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጠዋል።
በቀጣይ ኮሌጁ ከሁሉም የድርጅት አሰሪዎች እና ሰራተኞች ጋር በቅርበት ለመስራት በእቅድ እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል።